የ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ የ መወዳደሪያ ዘርፎች


የ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ የ መወዳደሪያ ዘርፎች

ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ እንደሌሎቹ የ ስፖርት አይነቶች የኦሎምፒክ ስፖርት ባይሆንም በተለያዩ ሃገራት የሚዘጋጁ ውድድሮች ግን አሉት በሃገር አቀፍ እና በ አለም አቅፍ ደረጃ። ኦሎምፒክ ላይ እንደሌሎቹ ስፖርቶች የመወዳደሪያ አይነት ያልሆነበት ምንም አይነት ጉድለትኖሮበት አይደለም ይሄ ነው የሚባል እርገጠኛ ምላሽ ባይኖርም እነደ ሃሳብ የሚንሰሱ ነገሮች አሉ  አንዱ የሰሜን ኮሪያ ከአለም ሃገራት ጋር ባላት የሻከረ ግንኙነት ሀገሪቱዋን በ ፖለቲካ ቁጥጥር ስር ለማድረግ ታስቦ ነው ይባላል አንዳንዶች ደግሞ የአለም ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌደሬሽን አንድ ሆኖ አለመጠናከር እና የእርስ በ እርስ አለመስማማት ነው የሚልም ነገር አለ።

     ያም ሆነ ይህ ስፖርቱ እንደ ስፖርት ምሉእ የሆነና በ አለም ሆነ በ ሃገር አቀፍ ውስጥ የሆነ የመወዳደሪያ ህግ እና ደንብ ያለው ስፖርት ነው።ሰለ ህግ ደንቦችን በቀጣይ ጊዜ የምቀርብ የሆናል።

ቴኳንዶ ስንት የመወዳደሪያ ዘርፎች አሉት?

ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ አምስት የመወዳደሪያ ዘርፎች አሉት።እነርሱም

 1. ፓተርን(pattern)
 2. ነጻ ፍልሚያ (fight)
 3. የተጠና ፍልሚያ (traditional sparing)
 4. ሃይል ሰበራ(power breaking)
 5. ልዩ ሰበራ(special breaking)

ፓተርንፓተርን የቴኳንዶ የጀርባ አጥንት እንደመሆኑ የአርቱ ሙሉ ነገር የምንማርበት የስፖርር መሰረታዊ ክፍል ነው።ፓተርን በግል እን በቡድን በመሆኑ ውድድር ሊደረግ ይችላል።ሆኖም ኝ ሁለቱም አይነት የወድድር ሲደረግ የረሱ የሆኑ መመሪያ እና መዳኛ ህግጋቶች አሉት።

ነጻ ፍልሚያ (Fight)- ይሄ ሁለተኛው የመወዳደሪያ አይነት ነው።ልክ እንደ ፓተርን ይሄም በነጠላ እና በግሩፕ ውድድሩ ሊካሄድ ይችላል።የነጻ ፍልሚያው በማካሄድበት ወቅት ሰውነትን ከከፍተኛ ጉዳት መከላከያዎች እንዲያደርጉ ያስገድዳል በሁለቱም የነጻ ፍልሚያ የውድድር አይነቶች እነርሱም

 • የጭንቅላት መከላከያ
 • የእጅ ጉዋንት
 • ውስጥ እግሩ ክፍት የሆነ የመወዳደሪያ ጫማ
 • የጥርስ መከላከያ
 • ለወንዶች ደግሞ የበልት መከላከያ ናችው።

የተጠና ፍልሚያ (traditional sparing)-ይህ የውድድር አይነት በሁሉት ሰዎች ልምምድ ተደርጎ እንደ ድራማ የሚቀርብ የውድድር አይነት ነው።ለእይታ አዝናኝ ከመሆኑ ባሻገር እራስን መከላከልና ማጥካትና የምንማርበት የውድድር አይነት ነው።ለመዳኘት የራሱ የሆነ ህኛ ድንብ አሉት።

ሃይል ሰበራ(power breacking)-ይሄ የውድድር አይነት በስፖርት ውስጥያሉ ተወዳዳሪዎች የሃይል እና የ ኢላማ ትክክለኛነት የሚለካበት ውድድር ነው።በሃገራችን  ችግር የሚታይበት የውድድር ዘርፍ ነው።አብዛኛው ተማሪ ከሰውነት ስለሚወጣ ሃይል እንጂ ስለ ትክክለኛ  ኢላማ የሚያስተውል የለም እና ከውድድሩ በሁዋላ አብዛኛው ተወዳዳሪ ከፍተኛ ለሆነ የ እጅ እና የ እግር ጉዳት ይዳረጋል>ለሴቶችና ለወንዶች የሚቀርበው የ ሚሰበረው ጣውላ መጠን የተለያየ ነው። ውድድሩ የሚካሄደው 5 በተመርጡ የስንዘራ አይነቶች ሲሆኑ 3 የ ኢግር እና 2 የ እጅ ስንዘራ ናችው።

እነርሱም

 • punch(ቡጢ)
 • sonkal yop terigi (በ እጅ ተረተር የሚደረግ ስንዘራ)
 • Doliyo chagi (በውስጥ እግር የሚደረግ ስንዘራ )
 • Yop chagi(በ እግር ተረተር የሚደረግ ስንዘራ)
 • Pande (በተረከዝ የሚደረግ ስንዘራ)

ልዩ ሰበራ(special breacking ይhሄ የውድድር አይነት ከሃይል ሰበራ የሚለየው የመወዳደሪያ የስንዘራ አይነቶች ናቸው።አምስቱም በ እግር የሚደረጉ ሲሆኑ በዚሀ የውደደር  አይነቶች ከተወዳዳሪዎች የሚጠበቀው ከፍታ እና ጣውላውን ሊሰብር የሚችል ትንስሽ ሃይል ነው።ቢሆንም ኝ ጣውላውን የሚስበርብት አካል ክፍል ትክክል ካልሆነ ከ ውድድሩ ያሰርዛል።


Leave a Reply