umpires in Taekwondo nanischool

የኢትዮጵያ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ አሶሴሽን የአለም አቀፍ የዳኝነት መመሪያ

የዚህ የዳኝነት መመሪያ አላማ ሁሉም ዳኞች መሪዎችን ለማወዳደር የሚያስፈልጋቸውን እውቀት እንዲገቡበት እና በውድድር ወቅት በእምነት፣ ህግና ደንብ መሠረት በመመራት አሠራራቸው ግልጽና አመቺ ለማድረግ ሁሉም ተወዳዳሪዎች ወይንም ተሳታፊዎች ከውድድሩ በኋላ የሚኖረውን ለማድረግ እና መሪዎች ከውድድር በኋላ መሸነፋቸውን አምነው እንዲቀበሉ ለማድረግ ታስቦ የተዘጋጀ መመሪያ ነው። አንደኛው ከሌላኛው ተወዳዳሪ የወንድማማችነት   እና የእህትማማችነት ውድድር እንዲሄድ በማድረግ ውድድሩ ጥሩ እና የተስሃለ ማድረግ ነው።ለዚሀም የዳኞች ሚና ከፍተኛ መሆኑ የታወቀ ነው ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት በሁሉም ዳኞች እየተሻለ እውቀት እንዲኖራቸው ታስቦ የተፃፈ መመሪያ ነው።

umpires in Taekwondo nanischool

የዳኝነት ስነ ስርዓቱ ውስጥ ማንኛውም ዳኛ ተወዳዳሪዎችን ለመዳኘት ከመግባቱ በፊት ሊፈጽማቸው የሚገቡ ቅደም ተከተሎች አሉ ይህም የትኛውም ውድድር ከመጀመሩ በፊት አለባበሳቸው ትክክል መሆን አለበት በኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ህግና መመሪያ መሰረት ማንኛውም ዳኛ ከላይ ነጭ ሸሚዝ ከተቻለ የቴኳንዶ አርማን የያዘ ከረባት ከስር ደሞ ጥቁር ሰማያዊ ሱሪ ማድረግ አለበት ሁሉም የዳኞች አባል ወደ ውድድር ቦታው በመግባት ቀጥ ያለ ሰልፍ ከያዙ በኋላ ቀኝ እጃቸውን በማንሳት ቃለ መሃላ ይፈጽማሉ። የቴኳንዶ መመሪያና ስነምግባር መርሆች እከተላለሁ።

 • የቴኳንዶ መመሪያና ስነምግባር መርሆች እከተላለሁ
 • የቴኳንዶ ክበብ ያለአግባብ በፍጹም አልጠቀመም
 • አስተማሪዎች  እና ታላላቆችን አከብራለሁ 
 • ነፃና ፍትሃዊ የሆነ መርህን እከተላለሁ 
 • ሰላማዊ የሆነች ዓለም እመሰርታለሁ 

አንድ ዳኛ ከሌሎች ዳኞቹንም ከአርት ባለሙያዎች የተሻለ ዳኝነት አቅም አለው ተብሎ መዘዘበት የራሱ የሆነ መመዘኛ አለው ከነዚህ ውስጥም መልካም ስነምግባር ያለው መሆን ግድ ይላል በተጨማሪምእራሱን በማንበብ ወይንም በመማር ከነበረው እውቀት ለመጨመር አዳዲስ ስልጠናዎችን ወስዶ ከነበረው እውቀት  ላይ ለመጨመር የሚጣጣር አይነት ሊሆን  ይገባዋል።ስለ ሰው ልጅ የሰውነት ክፍል በቂ እውቀት ያለው ከፖለቲካ ገንዘብ ከሙስና የፀዳ አስተሳሰብ ያለውና በቀለም ትምህርት ከሌሎቹ የተሻለ ቢሆን ተመራጭ ነው።የቴኳንዶ ስፖርትን ለማስፋፋት የእራሱን ጥረት የሚያደርግ እና በተጨማሪም ለማወዳደር ሰዎችን ያለምንም የኋላ ታሪክ ማለትም በሃይማኖት ለብሔር ወይንም በፖለቲካ አመለካከት ሳያስገባ በራሱ በሠራቸው እና በሚያቀርቡት ነገር በመገንዘብ ብቻ አንዱን ከአንዱ የሚያበላልጥ ወይንም የሚያወዳድር ፍትሀዊ ዳኛ መሆን አለበ።በ ውድድሮች ወቅት  የምንጠቀማቸው የኮሪያንኛ መግባቢያ ቃላቶች

ቼሪዮት ማለት ሰላምታ ለመስጠት እራስን ዝግጁ አድርግ ማለት ነው 

ጉክኔ በአክብሮት ሰላምታ ስጥ ማለት ነው 

ቹምቢ ማለት ደሞ ተዘጋጅ ወይም የሚሰጥ ትእዛዝ ተቀብሎ ወደ ቀጣዩ ስራ ሰውነትን ዝግጁ አድርግ ማለት ነው

ጃክ ማለት ጀምር ወይንም እንደ ማስነሻ እንዲሚጀመር የምንሰጠው ፃዝ ነው  

 ሄቾ ይህንን ትእዛዝ ደሞ የምንጠቀመው ነጻ ፍልሚያ ወቅት ሁለት ተወዳዳሪዎች እጅ ለእጅ በመያያዝ ወይንም በሚተቃቀፉበት ሰዓት ተላቀቁ ወይንም የተያያዙትን ነገር አቁሙ ለማለት  የምንጠቀመዉ ነው በተጨማሪም በ ነጻ ፍልሚያ ወቅት አንዱ ተወዳዳሪ በተወሰነለት የውድድር መስመሩ ከወጣ በዋላ አጥቂውተወዳዳሪ ተከትሎ ሊያጠቃው ሲል እንዲያቆም ትዛዝ ለማስተላለፍ እንጠቀምበታለን።

ጌሶክ ይህ ትዛዝ ደሞ በሆነ ምክንያት ውድድሩ ለሰከንድ ወይንም የሆነ ጥፋት ከተሰራ በኋላ ያጠፋውን ተወዳዳሪ ከ ተቀጣ በኋላ ከቆመበት ቀጥል ለማለት የሚሰጥ የ ትዛዝ አይነት ነው።

ጎማን ይህንን ትእዛዝ ደገሞ የምንጠቀመው ተወዳዳሪዎች ውድድሩን እንዲያቆሙ ትዕዛዝ ለመስጠት ነው። ነፃ ፍልምያ ከሆነ ሰአት አልቋል እና ውድድራቸውን አቁሙ ለማለት  እንጠቀምበታለን በፓተርን ውድድር ላይ ከሆነ ደግሞ ሁለቱም ተወዳዳሪዎች የመጨረሻውን እንቅስቃሴ ሰርተው ካቆሙ በሁዋላ ወደ መጀመሪያ ከእንቅስቃሴው ወይንም ወደ መነሻ ቦታ ተመለስ የሚል ትዛዝ ለማስተላለፍ እንጠቀምበታለን።

በ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶዳኝነት ውስጥ የምንጠቀማቸው ሁለት የቅጣት ትእዛዞች

 በ አብዛኛውን ጊዜ እነዚህን ሁለት የቅጣት ትእዛዞች ምን ጠቀማቸው በነጻ ፍልሚያ ውድድር ላይ ነው

ጁኢ  ማለት ለማስጠንቀቅ የምጠቀምበት የቅጣት አይነት ነው ጥቅሙ ማስጠንቀቅ ብቻ ሳይሆን ሶስት ጊዜ ማስጠንቀቂያ ካገኘ አንድ ሙሉ ያስቀንሳል ማስጠንቀቂያ የሚያሰጡት ቤቶች ከብዙ በጥቂቱ የሚከተሉት ናቸው።

 •  ፍልምያ ወቅት ተወዳዳሪ ከተፈቀደው ቦታውች ማጥቃት
 •  መሬት ላይ መውደቅ 
 • ከተፈቀደው የመወዳደሪያ መስመር ውጪ መሆን 
 • ያልተፈቀደ ቴክኒክ ወይንም ስንዘራ መጠቀም 
 • ሰዓት አለማክበር 
 • ዳኛ የሚሰጠውን ትዕዛዝ አለመስማት  ከብዙ ጥቂቶቹ ናቸው።

ጋምጁ ይሄ ቅጣት ደግሞ ተወዳዳሪው ሙሉ ነጥብ እንዲቀነስ የሚያደርግ ጥፋት ሲያጠፋ የምንጠቀምበት የትእዛዝ አይነት ነው። በፍልሚያ ውድድር ወቅት ሙሉ ነጥብ የሚያስቀንሱ ጥፋቶች አሉ። 1ሙሉ ነጥብ  ከመቀነሱ በላይ 3 ሲሞላ  ሙሉ ለሙሉ ከውድድር ያሰርዛል።አንድ ተወዳዳሪ በነፃ ፍልምያ ወቅት ሦስት ጊዜ ጋምጁ የሚል ቅጣት  ከተሰጠው ከውድድሩ በቀጥታ ይሰረዛል ምንም ያህል ውድድሩን እየመራ ቢሆን

 • ሙሉ ለሙሉ ከውድድር ወቅት አንድ ሙሉ ነጥብ የሚያስቀንሱ ጥፋቶች 
 • ሃይል በተቀላቀለበት መልኩ ለማጥቃት መሞከር 
 • ከፈቀደ ቦታ ውጪ በከፍተኛ ሀይልማጥቃት 
 •  የኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ህግና ደንብ መሰረት ለማጥቃት ያልተፈቀደ ቦታ ማጥቃት
 •  በኢንተርናሽናል ቴክዋንዶ ህግና ደንብ መሰረት ለማጥቃት ያልተፈቀዱ የ ስንዘራ አይነቶችን መጠቀም ተመሳሳይ አይነት ጥፋትን በተደጋጋሚ ማጥፋት
 •  ከዳኛ ጋር ያለአግባብ ወይም በስሜታዊነት መነጋገር ከብዙዎቹ በትንሹ ናቸዉ።

ሲልኪዮክ ማባረር 

ሆንግ ቀይ መአዝን

ቾንግ ሰማያዊ መአዘን

ጁንግ ጂ ሰአት ይቁም

ዶንግቾን እኩል

ኢልሁ ጆንግ 1ኛ ዙር

አይ ሁዶንግ 2ኛ ዙር

ሳም ሁጃንግ 3ኛ ዙር

ሱንግ አሸናፊ

በዛሬው ጽሑፍ ላይ ይህን ያህል ከተባባልን በቀጣይ ጽሑፍ ላይ ደሞ የተቀሩትን በዳኝነት ውስጥ የምንጠቀማቸውን ቃላትና እያንዳንዱን የነጥብ አያዝ ግልጽ በሆነ አማርኛ ለማስረዳት እሞክራለሁ አመሰግናለሁ።

Leave a Reply