belet

በኢንተርናሽናል ቴኳንዶ የቀበቶ ትርጉም

በኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ሁሉም የቀበቶ ደረጃዎች ትርጉም አላችው።ስድስት የ ከለር ቀበቶ እና ከ አንደኛ ዲግሪ እስከ ዘጠነኛ ዲግሪ ደረጃዎች አሉ ።እንዚሀ የከበቶ ደረጃዎችበ ቴኳንዶ ውስጥ እንደማረግ የሚያገለገሉ ሲሆነ አነደኛወን ተማሪ ከ አነደኛው በደረጃ ለመለየትም ያገለግላሉ።በኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ሁሉም የቀበቶ ቀለማት የየራሳቸው ትረጉም አላችው።

ቀበቶ የማሰር ትርጉም

በኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ቀበቶ ማሰር የራሱ የሆነ ተረጉመ አለው።አበዛኛው ጊዜ ቀበቶ የሚታሰረው አንደ ዙር ንው ይህም ተክክል ሆኖ ሳለ አንዳንድ ሰዎች ባለ ማወቅ ሁለት ዙር ቀበቶ ያስራሉ ይህ ትክክል አደለም ምክንያቱም  በ አርቱ ህግ እና ከ ቀበቶ ትርጉም ጋረ ሰለሚጣረስ ነው።ቀበቶ አንድ ዙር እሚታሰረው አንድ የ ቴኳንዶ ተማሪ ለ አንድ አሰተማሪው እንደሚግዛና አንድ አላማ እንዳለው የሚያሳየ ነው።ቀበቶው በሚታሰርበትም ወቅት ልክ እንደ ከረባት ያራሱ የሆነ የ አስተሳሰር ስርአት  አለው።

የከለር ቀበቶ ደረጃ ትርጉም

ነጭ ቀበቶይሄ የመጀመሪያ ወይም አንድ ተማሪ የ በኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ለመሰራት ወደ አዳራሽ ሲሄድ የሚሰጠው የ ቀበቶ ደረጃ ነው ።ትርጉሙም ለ ስፖርቱ አዲስ እንደሆነና ሰለ ስፖርቱ ምንም አይነት እወቀት የሌለው ማለት ንው ።በ ነጭ ወረቅትም የመሰላል።

ቢጫ ቀበቶ-ይሄ የቀበቶ ደረጃ በኢንተርናሽናል ቴኳንዶወጥ ትንሽ ጊዜ የሰራና ስለ በኢንተርናሽናል ቴኳንዶ መሰረታዊ እውቀት ያለው የሚመሰለውም በተክል ስር ነው። አንድ ተክል ተተክሎ ከ መሬት ጋረ ተጣብቆ ወደፊትም በሚያድግበት ወቅት ጥንከሮ እንዲቆም ስር ያወጣል በስፖርቱም እንደዛ ነው አንደ ስፖርተኛ ወደፊት በቀጣይነት ጥንክሮ እንዲቆም እና ያሰበበት ቦታ እንዲደርስ መሰረት የሚይዝበት የ ቀበቶ ደረጃ ነው።

አረንጓዴ ቀበቶ- አንድ ተማሪ እዚህ የቀበቶ ደረጃ ላይ ሲደርስ ስለቴኳንዶ በመጠኑ ያወቀ እና ወደ ከፍተኛ ደረጃ ለመደረስ በመንደርደር ላይ ያለ ተደርጎ ይታሰባል።የሚመሰለውም በቅጠል ነው።አንድ ተክል ተተክሎ ስር ከያዘ በሁዋላ ከጣይ የሚያወጣው ቅጠል ነው በዚሀም ተምሳሌት መሰረት አንድ ተማሪ  አረንጓዴ ቀበቶ አሰረ ማለት ከ ቢጫ የተሻለ ነገር እንዳለው እና ወደ ቴኳንዶ በጠልቀት ለመግባት እየተንደረደረ እንዳለ ተደርጎ የወሰዳል።

ሰማያዊ ቀበቶ-ይህ የቀበቶ ደረጃ ላይ የደረሰ ተማሪ ስለቴኳንዶ ስፖርት በቂየሆነ እውቀት ያለው እና ከራሱ አልፎ ለሌሎች ማስተማር የሚችልው እውቀት ያለው እንደሆነ የታሰባል።ሰማያዊ ቀእቶ በ ባህር እና በ ሰማይ ይመሰላል ማለትም  አንድ ተማሪ ሰማያዊ ቀበቶ አለው ማለት በ ስፖርቱ እነደባህር የጠለቀ እና እንደሰማይ የራቀ እውቀት  እንዳለው ተደርጎ ይቆጠራል።

ይ ቀበቶ-ይህ የቀበቶ ደረጃ ከሁሉም የተሻለ ፈጣን እና ቀልጣፋ ለሚፈጠሩት ነገሮች ሁሉ በ አፋጣኝ ምላሽ የሚሰጥጠንቃቃ የሆነ ሙሉ በሙሉ በራስ መተማምን ያለው ቴኳንዶን በደንብ የተረዳ ተማሪ ማለት ነው።ቀይ ቀበቶም በ እሳት ይመሰላል።

ጥቁር ቀበቶ- ይህ የቀበቶ ደረጃ የተረጋጋ እና ሰለ ስፖርቱ ጥልቅ እውቅት ያለው እና ለሚፈጠሩት ነገሮች ሁላ በተረጋጋ መንፈስ ነገሮችን በማሰተዋልና በተረጋጋ ሰሜት የማያዳግም ምላሽ እንደሚሰጥ የታሰባል። የሚመሰለውም በ ጨለማ ነው።ሙሉ የሆነ እራሰን የመግዛት እና አስተዋይነትን የተላበሰ እንደሆነ ይታመናል።

ከ እዚህ በመቀጠልም ከ 1 እሰከ 9 ዳን ድረስ ያሉትን ትርጉም በለላ ልጥፍ እነገናኝ እኔ ለዛሬ ጨርሻለሁ ለ ማርሻል አርት ቤተሰብ ግን ይሄን ጥያቄ ላስቀምጥ እውነት በወገባችን ላይ ያለው ቀበቶ እየሰራን ያለውን ይገለጻል ይሄን ለሁላችን ጥያቄ ይሁንና እራሳችንን በ ማስተዋል እንመልከት።

Leave a Reply