taekwondo in Amharic

የቴኳንዶ ጥቅሞች

የቴኳንዶ ጥቅሞች

ቴኳንዶ ጥንካሬን እና ተጣጣፊነትን የሚገነባ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ የአካል ብቃት እና ደህንነትን በእጅጉ የሚያሻሽል የታወቀ  ስፖርት ነው። ቴኳንዶ እንዲሁ እንደ ራስን መግዛትን ፣ተወዳዳሪነት፣ ማህበራዊ ክህሎቶችን እና ሌሎችንም ብዙ ሌሎች ክህሎቶችን እንድናዳብር ያግዘናል።ከሚሰጡተም ጥቅሞች መካክል ጥቂቶቹን በመጥቀስ ለመወያየት እንሞክር

የጥንካሬን ክህሎቶችን ይገነባል

ሁላችንም ትምህርት ስንጀምር መሰረታዊ ነገሮችን በመማር እንደነበር ይሚዘነጋ አደለም ፣ በሁሉም የዕድሜ ደረጃ ፣ እና ችሎታዎች ተማሪዎች ቅልጥፍናን ፣ ሚዛንን  መጠበቅን እና ሰውነትን መቆጣጠር መሰረታዊ ከሚባሉት በመጀመር ይማራሉ ። ተማሪዎች በሚያሠለጥኑበት ጊዜ አዳዲሰ እና ከዚህ በፊት የማይታወቁ የቴክኒክ እና የታክቲክ ክህሎቶችን ያዳብራሉ። በተጨማሪም… በዋና ጥንካሬ ፣ በጡንቻ ጥንካሬ ፣ የልብና የደም ቧንቧ ጽናት እና ተጣጣፊነት በተሻለ ሁኔታ እንዴት እንደሚሠሩ እና ምን አየነት ቴክኒክ እንደዛ አይነት ጥንካሬ እንደሚሰጡም በግልጸ ይማራሉ።

የመዝናኛ ስፖርት

ቴኳንዶ በዓለም ውስጥ በጣም ተወዳጅ ፣ ተለዋዋጭ እና በሰፊው የሚተገበር የማርሻል አርት ነው። የውድድር ስፖርት ስለሆነም ቴኳንዶ ከሚሰራው ሰውም በተጨማሪ ውድድሩን ለሚያየው ሰው የበለጠ አስደሳች እና ፈታኝ እንደሆን እያየ የሚዝናናበት የ ማርሻል አርት ስፖርት አይነት ።

ማህበራዊ ክህሎቶችን ያሻሽላል

በአሁኑ ወቅት ሰዎች ጊዜያቸውን በማህበራዊ ሚዲያችን እና በቴክኖሎጂ ላይ እያጠፉ ይገኛሉ ይህም በሰዎች መሃል ያለው የ ማህበራዊ ክህሎቶች ልውውጥ እንዲጠፋ ምክንያት ሆኑዋል ሆኖም ግን ይህን ለማስተካከል ስፖርት በዚህ ረገድ ትልቅ ሚና ። ብዙዎች በአይፓድ ፣ በሞባይል ስልኮች እና በ ጌም ላይ ተጣብቀዋል። የ ቴኳንዶ ስፖርት ግን ማህበራዊ መስተጋብርን እና የ እርስ በርስ ግልጽ ግንኙነት እንዲዳብር ቴኳንዶን እንደ መሣሪያ እንጠቀማለን። ሁሉም ስፖርተኛ  ሰው አክባሪ እና ጨዋ እንዲሆን ፣ ራስን መግዛትን ፣ ስነምግባርን ፣ እና ወደ ስኬት የሚያመሩ ጥሩ ወጥ የዕለት ተዕለት ልምዶችን እንዲያዳብር ስልጠና ይወስዳል ምክንያቱም ስፖርተኛ ለመባል እንዚህን ነገሮች እንደግዴታ የሚታይ ነገር ነው።

የአእምሮ ችሎታን ይጨምራል

የሥራ ሥነ ምግባር ፣ ቆራጥነት ፣ ጽናት ፣ እቅድ እንዴት ማውጣት እና ማሳካት እንደሚችሉ ይማራሉ። ይህ የሚከናወነው በትኩረት ፣ በመደጋገም ፣ በቁርጠኝነት እና በቋሚነት ተግባሮችን ፣ ክህሎቶችን ወይም ልምምዶችን በመለማመድ ነው። ለጤነኛ እና አምራች አእምሮ ፣ አካል እና መንፈስ ሚዛንን ስለሚሰጥ በሁሉም ዕድሜ ያሉ ተማሪዎች ከቴኳንዶ ስልጠና በከፍተኛ ሁኔታ ይጠቀማሉ።

የመንፈስ ጥንካሬ እንዲያገኙ ያግዛል

ማንኛውም የ ስፖርት አይነት በደግግሞሽ ሰልሚሰራ በተጨማሪም ሰውነትን ወይም የአካል ክፍልን ሰለሚፈትኑ በነዚህ የስልጠና ድግግሞስህ ሂደቶች ውስጥ የመንፈስ ጥንካሬን እንዲያዳብሩ እና እንዲማሩ ያረጋል።

በመጨረሻም እንዚህ ከላይ የተጠቀሱት ለማንኛውም የ ስፖርት አይነት በምንሰራበት ወቅት የምናገኘው ጥቅም እንጂ በ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ስፖርት ስልጠና ወቅት ብቻ የምናገኘው ጥቅም  አደለም  በ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ስፖርት ስልጠና ደገም እንደ ስፖርቱ ፍልስፍና የምናገኘው ጥቅም አለ በቀጣይ በዚያ ዙሪያ ሃሳብ ይዤ ይመጣል።

Leave a Reply