nanischool

የቴኳንዶ ታሪካዊ አመጣጥ

ቴኳንዶ ማለት ያለምንም መሳሪያ እጅና እግር በማጣመር የሚሰራ አንደኛው ጥንታዊ የማርሻል ስፖርት አይነት ነው።ቴኳንዶ  የሚለውን አርት ከመፈጠሩ በፊት በ ኮሪያ ጥንታዊ የሆነ  አርት ነበረ እርሱም “ቴኪዮ” ይባል ነበር ።ይህ የኮሪያ ጥንታዊ አርት ቴኳንዶ የሚባለውን አርት ለመፈልሰፍ ትልቅ እገዛ አድርጉዋል ምክንያቱም ጀነራል ቾይሆንግ ሂ ቴኳንዶን ከመፈልሰፋችው በፊት ቴኪዮን ና የ ጃፓን  ካራቴ አጣምረው ያጠኑ እንደነበር የታሪክ መዛግብት ያብራሩልናል።ይህ ቴኪዮየተባለ ጥንታዊ አርት ከ50 B.C በፊት ጀምሮ ነበር።በዚያን ወቅት በኮሪያ በ 3 ጎሳዎች አመራር ተከፍላ ነበር።እነርሱም

  • Silla(ሲላ)
  • Kagoriyo(ክጎርዮ)
  • Paekche(ፓክች) ይባሉ ነበር።

ይህ ቴኪዮ የተባለ አርት በ አሁኑ ደቡብ ኮሪያ ‘’ሱባክ’’ የሚል ሰያሜ ነበረው። በተጨማሪምየ አርት በ ሲላ ጎሳ ውስጥ በጣም ተወዳጅ ነበር ከ 668-935AD ቴኪዮ የተሰኝው ስም በ ኮጎርዮ ጎሳ 935-1392 ስሙን ሱባክ ወድሚባል መጠሪያ ቀይረውት ነበር።

   የመጀመሪያ ስለ ሱባክ የሚያትት መጽሃፍ ለ አለም ህዝብ የተዋወቀው በ  “ዩ ጎሳ”ነበር ከ1337-1907 ይሄ መጸሃፍስለ ሱባክ አርት በጣም ጠቃሚመረጃዎችን ይዞ እንደነበር ይነገራል ሰዎችህ የነበራቸውን ጥቂት እውቀት በሰፊው ያብራራ ነበር።ይህን አርት እንዲሰሩ የሚፈቀደው ግን ለ ወታደሮች ብቻ ነበር ነገር ግን “ዩ ጎሳ”ሊወድቅ አካባቢ አርቱ ወደ ማህበረሰቡ ተሰራጭቶ እንደነበር ይነገራል።

 ብ1909 ጃፓኖች ኮሪያን በቀኝ ግዛት በያዙበት ወቅት ሱባክ የሚባለወን አርት እና የተለያዩ የ ኮሪያን ባህል ከነሱ ከተማሩ በሁዋላ አርቱ እንዳይስፋፋ አርቱን የሚያቁትን ትልልቅ አስተማሪዎችን ከገደሉ በሁዋላ መጻሃፎችሁንም አቃጠሉዋችው ከዚያም በሁዋላ ሱባክ የተሰኘው ባህክላዊ አርት ተወዳጅነቱን እያጣ ሄደ።

ጃፖኖች ኮሪያን ለቀው ከወጡ በሁዋላ  ሱባክ የተሰኝውን አርት  ከ ቻይና ባህላዊ አርቶች ጋር በማጣመር  ጁዶ(judo)ካራቴ(karate) እና ኩንጉፉ(kungufu) የተባሉ አርቶችህ ተፈጥረዋል።

የመጀመሪያው በኮሪያ የ ማርሻል አርት ትምርትቤት ‘’ክዋን’’ ይባል ነበር ከ 1945 ሁለተኛው የ አለም ጦርነት ማብቂያ በሁዋላ ብዙ የ ማርሻል አርት ትምርት ቤቶች ሊከፈቱ ችለዋል።እንዚሀም የማርሻል አርት ትምርትቤቶች የሚያስተምሩት የኮሪያ ባህላዊ አርትን ሱባክን ነበር ።ከዚያም በሁዋላ ጀነራል ቾይሆንግ ሂ የጃፓን ካራቴን እና ቴኪዮን በቀድሞ ስሙ ሱባክ የሚባለውን በማጣመር  ቴኳንዶ የሚለውን አርት ለመፍጥር ችለዋል።

   መጋቢት 11 1995 የኮሪያ ማህበረሰብ የሚወክሉ ሰዎች ማስተሮች ቦርድ እና የታሪክ ባለሞያዎች አንድ ላይ በመሆን ለ ኮሪያ ባህል ተስማሚ የሆነ ስያሜ ለመስጠት ስበሰባ አደረጉ ከዚያም በ ጀነራል ቾይሆንግ ሂ የተመረጠው ቴኳንዶ የሚለው ሰያሜ  ተመረጠ ይህም ስያሜ ሚያዛ 11 1995 ህጋዊ ሆነ።በዚያወም አመት ጀነራል ቾይሆንግ ሂ  የ ኮሪያ ቴኳንዶ ማህበር ፕሬዘዳንት  ሆነው ተመረጡ።ከ  7 አመት በሁዋላመጋቢት 22 966 አም የ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፌደሬሽን ለመመስረት ችለዋል ከዚያም እራሳችው የ ፌደሬሽኑ  ፕሬዘዳንት በመሆን አገልግለዋል።የ ኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፕሬዘዳን እንደመሆናችው መጠን አረቱን በ አለም ሁሉ በመዞር ለማስተማር ሞክረዋል ነገር ግን በ 2002 እኤአ በ ካንሰር ምክንያትም ከዚህ አለም በሞት ሊለዩ ችለዋል።በ አጭሩ የ የቴኳንዶ ታሪካዊ አመጣጥ የሄን ይመስላል።

2 Comments

Leave a Reply