taekwondo in Amharic

የቴኳንዶ አስተማሪ ምን መምሰል አለበት

እንደሚታወቀው ቴኳንዶ አንዱ የማርሻል አርት ስፖርት አይነት ነው።ስሙ እንደሚያመለክተው ማርሻል አርት ማለት ደግሞ ወታደራዊ ስርዓት ወይንም ጥበብ እንደማለት ነው። በመሆኑም የቴኳንዶ ስፖርት ከወታደራዊ ስነስርአት የሚጋሯቸው ብዙ ነገሮች አሉ። አንድ የወታደር ቡድን ወይንም ብርጌድ ብቃቱንና ስኬቱ የሚለካው በሚመራው ወታደር ነው።ጥሩ መሪ እስካለ ድረስ ጥሩ ተመሪ መፍጠር ያን ያህል አዳጋች አይሆንም።

taekwondo instructor

በቴኳንዶ ስልጠና ወቅትም ያለው ይህ ነው ጥሩ አስተማሪ እስካለ ድረስ ጥሩ ተማሪዎችን ማፍራት ያን ያህል አስቸጋሪ አይሆንም ወደሃገራችን የቴኳንዶ አስተማሪዎች ስንመጣ ግን የተዋጣለት ተማሪ እንጂ እሱም በጣም ጥቂት ብቁ አስተማሪ አለ ለማለት አያስደፍርም ይህም የሆነበት ምክንያት ስፖርቱን የሚያሰለጥኑት እንደ ስራ እና እንደ ገቢ ምንጭነት ብቻ በመቁጠር ለሚሰሩት ነዉ።የኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፈልሳፊ ጄነራል ቾይ ሆንግ ሂ ብቁ አስተማሪ(ideal Instructor) ማሟላት አለባቸው ብለው ያስቀመጣቸው ስምንት ነጥቦች አሉ ግን እንደ አጠቃላይ ደግሞ በቴኳንዶ ውስጥ ብቁ አስተማሪ እና ብቁ ተማሪ ለመባል እነዚህን ሁለት መሰረታዊ ነገሮችን አዋህዶ መጠቀም ግድ ይላል እነሱም የመንፈስ ጥንካሬ እና በቴኳንዶ ውስጥ ያሉትን ቴክኒኮች በደንብ መረዳት ናቸው።ለማጠቃለል ያህል የኢንተርናሽናል ቴኳንዶ ፈልሳፊ ጄነራል ቾይ ሆንግ ሂ ያስቀመጡትን 8 ጠንቃራ አስተማሪ መለኪያዎች የምንላቸውን ዛሬ ላስተዋውቃችሁ እሞክራለሁ

  1. ጠንካራ የሞራልና የስነ ምግባር ባለቤት የሆነ
  2.  ግልጽ የሆነ አቋም እና ህይወት ፍልስፍና ያለው
  3.  ኃላፊነት ለመውሰድ እና ለመፈጸም ዝግጁ የሆነ
  4.  በቴክኒኮች ዙሪያ ጠያቂ እና ተመራማሪ የሆነ
  5. ስለ ሰው  ልጅ ስራአተ ሰውነት አካል ጥቅም እና የአሠራር ሂደትን ጠንቅቆ የተረዳ
  6.  በፖለቲካ እና ጉዳዮች ላይ ታማኝና አገኘ የሆነ
  7.  የቴኳንዶ አርት በዓለም ዙሪያ ለማሰራጨት ዝግጁ የሆነ
  8.  የአዛውንቶች የሚመሰገን በ ባልደረቦቹና ጓደኞቹ ወይንም አስተማሪዎቹ የሚታመንና የሚወደድ ናቸው።

እና ስንቶቻችሁ አስተማሪዎች ናችሁ ይሄንን ያላችሁ ወይንም የተባለን የምትፈጸሙ ይሄ ለሁሉም አስተማሪዎች የሚቀርብ ጥያቄ ነው።

Leave a Reply