training secreta of taekwondo by nanischool

በቴኳንዶ ስልጠና ወቅት ማውቅያለብን ሚስጥሮች

በቴኳንዶ ውስጥ የሚሰጠው ሥልጠና ከስፖርት ቤት ስፖርት ቤት ቢለያይም መሰረታዊ ነገሮቹ ግን አንድ አይነት ነው ።እነርሱም ፓትርን፣በነጻፍልሚያ ወቅት ያለው ቴክኒክና ህጎች፣ራስን መከላከል ፣ የመስበር ቴክኒኮች በጣም የሚለየው ግን በእያንዳንዳቸው መሰረታዊ ነገሮች ውስጥ የሚሰጠው ትኩረት እና የ አሰለጣጠን ዘዴ ነው። አንዳንድ ተማሪዎች ስፖርትን ደጋግመው ይሰራሉ  ጥረት የደርጋሉ ​​ነገር ግን ዘላቂነት የለውም ። አንዳንድ ጊዜ “በቶሎ ለመሻሻል ምስጢሩ ምንድነው?” ብለው ይጠይቃሉ። አንድ ሰው ከተራ ስፖርተኛ ወደ የተሻለ ስፖርተኛ ለመሄድ  ምን ማርግ እንዳለብን ግራ የሚገባቸውም ብዙዎች ናቸው ነገር ግን የተሻለ ስፖርተኛ ለመሆን ምስጢሩን ማወቅ ያስፈልጋል።

ጄኔራል ቾይ ሆንግ ሂ ባሳተሙት በ 15 ጥራዝ ኢንሳይክሎፔዲያ ውስጥ ሁሉም  መልሶች አሉት። በቴክኳንዶ ውስጥ ባለሙያዎች ራሳቸውን ለማሻሻል የሚጠቀሙባቸውን 7 “የሥልጠና ምስጢሮች” እንዳሉ ይነገራል። ብዙውን ጊዜ እነሱን አንብቦ መረዳትሊከብድ የችላለ ከ ብዛቱ አንጻር  ስለዚህ አጭር ማብራሪያ እንደሚከተለው ለማስቀመጥ ሞክሪያለሁ።

1) የኃይል ንድፈ ሀሳቡን ጠንቅቆ መረዳት

ያለ ኃይል የእኛ ቴክኒክ ዋጋ የለውም! የተለያዩ የኃይል ዓይነቶችን በማጥናት እያንዳንዱን ቴክኒክ የበለጠ ዋጋ ያለው ማድረግ እንደምንችል እንማራለን። ኃይለኛ ብሎኮች ከትላልቅ እና ጠንካራ ስንዘራዎች ሊጠብቁን እና ኃይለኛ ስንዘራዎች  በተመሳሳይ የበለጠ ጉዳት እንዲደርስ ያስችለናል።

2) የእያንዳንዱን እንቅስቃሴ ዓላማ እና ትርጉም በግልፅ መረዳት

እያንዳንዱን እንቅስቃሴ ሳይረዱ የእኛ ቴክኒኮች ውጤታማ ላይሆኑ ይችላሉ። አራት ማዕዘን ቅርጾችን ወደ ክብ ቀዳዳ ለማስገባት ከመሞከር ጋር አንድ አየነት ልፋት ነው የሚሆነው የእንቅስቃሴ ዓላማ እና ትርጉም በግልፅ ሳይረዱ ለመስራት መሞከር ። ትክክለኛውን እንቅስቃሴ በመረዳት ለማጥቃት ወይም ለመከላከል መሞከር የምንፈለገውን ውጤት እንድናገኝ ይረዳናል።

3) የአይን ፣ የእጆች ፣ የእግሮች እና የትንፋሽ እንቅስቃሴን ወደ አንድ የተቀናጀ እርምጃ እንዲያርፉ ማድረግ

  እያንዳንዱን የሰውነት ክፍል ወደ አንድ የተቀናጀ እንቅስቃሴ ማምጣት ስንማር የበለጠ ኃይል እንፈጥራለን። ዓይኖቻችን ወደ ትክክለኛ ዒላማ ላይ ያተኩራሉ ፣ እጆቻችን በማጥቃት እና በመከላከል ወቅት ኃይል ይፈልጋሉ ፣ እግሮቻችን መሬት ላይ እንደንቆም  ብቻ አይደሉም ነገር ግን የበለጠ ኃይል ለማግኘት የ እነሱ አስተዋጾ ቀላል አይደለም ፣ እና እስትንፋሳችን አዕምሯችንን እንድንሰበስብ፣ትኩረት እንድናረግ  እና ከፍተኛ የታመቀ ሃይል እንድናወጣ ይረዳናል። ከፍተኛ ኃይል እንዲወጣ በተዋሃደ አቅጣጫ ሁሉም የሰውነት ጡንቻዎች መሳተፍ አለባቸው።

4) ለእያንዳንዱ ወሳኝ ቦታ ተገቢውን የማጥቂያ ቴክኒክ መምረጥ

የድሮው አባባል “ያለዎት ብቸኛው መሣሪያ መዶሻ ሲሆን ሁሉም ነገር ሚስማር ይመስላል!” ነጋዴዎች ለተለያዩ ሥራዎች የሚጠቀሙባቸው የተለያዩ መሣሪያዎች እንዳሏቸው ሁሉ እኛም ለተለያዩ ኢላማዎች የተለያዩ የማጥቂያ እና የመከላከያ ቴክኒኮች አሉን እንደሚያስፈልገው ቦታ ተገቢወን መጠቀም ወደ ተሻለ ስፖርተኛነት ይቀይረናል።

5) ለጥቃት እና ለመከላከያ ከትክክለኛው ማእዘን እና ርቀት ጋር ማዋሃድ

በስልጠና እና በልምድ በኩል አንግል እና ርቀትን እንማራለን። እኛ በጣም ሩቅ ከሆንን ከክልል ውጭ ነን እና በጣም ቅርብ ከሆንን በቂ ኃይል መፍጠር አንችልም ወይም የምንፈልገወን ቴክኒክ መጠቀም አንችልም።

6) እንቅስቃሴ በሚንቀሳቀስበት ጊዜ ሁለቱንም እጆች እና እግሮች በትንሹ እንዲታጠፍ ማድረግ

የሰውነታችንን እጆች እና እግሮች ቀጥ ብለን ስንይዝ ጡንቻዎቻችን ጥብቅ ናቸው። በትንሹ በማጠፍ ዘና ለማለት እድል እናገኛለን ይህም ፍጥነትን እና ሃይልን ለመፍጠር ይረዳል። በመካከል ቴክኒኮች መካከል ዘና ማለት በጣም አስፈላጊ ነው።

7) የጉልበቱን ምንጭ በትክክል በመጠቀም በእንቅስቃሴው ወቅት የተሳለ ሃይል ማውጣት

የ ውቂያኖስ ሞገድ ወደ ታች ፣ ከዚያ ወደ ላይ ፣ ከዚያ እንደገና ወደ ታች ይጓዛል። በ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ውስጥም ያለው ይህ ነው በተለይ ፓተርን ላይ ይህ የሆነበት ምክንያት ሰውነታችንን ይዘን ወደላይ ስንወጣ ሰውነታችን ዘና ለማለት ጊዜ ያገኛል ወደታች ስንወርድ ደግሞ የተሻለ ሃይል እንድናመነጭ ይረዳናል ማለት ነው።

በስተመጨረሻም እነዚህ የሥልጠና ሚስጥሮች የሚከተሉትን ጨምሮ በሁሉም የቴኳንዶ  ስልጠናዎች ላይ ይተገበራሉ-ማለትም ፓትርን፣በነጻፍልሚያ ወቅት ያለው ቴክኒክና ህጎች፣ራስን መከላከል ፣ የመስበር ቴክኒኮች። በስልጠናችን ላይ እነሱን መተግበር የተሻለ ስፖርትርኛ ከመባላች በተጨማሪ በቁ ተወዳዳሪ እንድንሆን ይረዳናል።

Leave a Reply